1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

DW Amharic የሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዜና መጽሔት

Eshete Bekeleረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2016

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ለተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች “ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፤ ለዚህ አንታገልም” ሲሉ ተናገሩ። በግጭት ምክንያት በአማራ ክልል ደም ባለመሰብሰቡ ሆስፒታሎች ሕሙማን ለማከም ችግር ገጥሟቸዋል። በትግራይ ክልል የሚገኘው እና በጦርነት ወቅት የተጎዳው የአል ነጃሺ መስጂድ መልሶ ለመገንባት ያቀደ መርሐ ግብር ይፋ ተደረገ። ኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት ባለፈው ዓመት ከነበረችበት በአስራ አንድ ደረጃዎች ወደ ኋላ አሽቆለቆች። እስራኤል በራፋ የጀመረችው ወታደራዊ ዘመቻ እንዳሳዘናቸው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/4fdu6
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-Zeitfunk-DWcom

ዜና መጽሄት

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪቃ፣ የአውሮጳ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜና ዘገባዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መጽሄት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል።